አሞኒ
ዘዳግና ዘናህሶ ኢትዮጵያዊ በየካቲት 5 ቀን ተወለደ ትውልድ ሀገሩ አክሱም ነው፡፡ በተወለደም ጊዜ ሰይጣናት የወላጆቹን ቤት ከበቡ
እሱም እንደተወለደ መንፈስ ቅዱስ ስለሞላበት በእጁ ቢያመለክት በአንድ ጊዜ 60 ሰይጣናት እንደ ጢስ በነው ጠፍተዋል፡፡ ተሸንፈዋል
ስለዚህም አሞኒ ተብሎአል፡፡ አሞኒ ማለት
አሸናፊ ማለት ነው፡፡ ይህ አባት የአባ ዩሐኒ የቆብ አሳዳጊ አባት ነው፡፡ እሱን ደግሞ በሰኔ 5 ቀን አባ ክርስቶስ ቤዛነ አመነኮሰው ይህ ጻድቅ የሰው ፊት ሳያይ 40 ዘመን ሙሉ የኖረና ከመላእክት ጋር ያመሰገነ ትልቅ አባት ነው፡፡ታሪኩ እንደሚለው እንጦንስ መቃርስን፣ መቃርስ ጳኩሚስ፣ ጳኩሚስ ቶወድሬስንና አቡነ አረጋዊን፣ አቡነ ክርስቶስ ቤዛነም፣ አቡነ መስቀለ ሞአን/አሞኒን/ አሞኒም መስቀለ ሞአም፣ አባ ዩሐኒን አባ ዩሐኒም አባ ኢየሱስ ሞአን፣ አባ ኢየሱስ ሞአም አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ያመነኩሳሉ እነዚህ በገሐድ የመጣ ሰይጣን ካልሆነ በስተቀር የታሪክና የሃይማኖት ሰው የሆነ ሁሉ በታሪክ ሊረሳቸው አይችልም፡፡ ቅዱስ አሞኒ በደመና ተጭኖ ሄዶ ደብረ ዘይት ከአባ እብሎይ ጋር የተገናኘ አባት ነው፡፡ የራሱ ፀጉር ልብስ መጎናፀፊያ ሆኖት የኖረ ልብስ አልነበረውም የመንፈስ ቅዱስ ልጁን አባ ዩሐኒን እሱ እያጫወተ አሞራ እያለበሰ ቶራ እያጠባቸው ያሳደገ አባትና ባለ ታሪክ ነው፡፡ ፃድቁ በተወለደ በ160 ዓመቱ በህዳር 5 ቀን አርፎአል፡፡ ከአባ ዩሐኒና ከአባ አበጊዶ ጋር 20 ዓመት ኖሮአል፡፡ በስሙ የተሰራው ገዳም በትግራይ ተንቤ ደብር አሣ ይባላል፡፡ ተራራው የአሣ ቅርፅ ያለበት ተራራ ነው፡፡ በደግና ቀበሌም አለው በዋሻ ውስጥ የተቀበረ ባለ ታሪክና የቤተ ክርስቲያን አስደናቂ ታሪክ ያለው ጻድቅ ነው፡፡ ጻድቁን ግብፃዊ ነውም ይሉታል ትውልዱን፡፡

No comments:
Post a Comment
ማህበረ ቅዱስ አሞኒ