"ለፈራሔ እግዚአብሔር
ይሤኒ ደኅሪቱ፣ ወይትባረክ ዕለተ ሞቱ"
"እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው
ፍፃሜው ያምራል፡፡ በሚሞትበትም ቀን ይከበራል" ሲራ. 1፡13፡፡
የብፁዕ
ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት የዓለም የሰላም አምባሳደር የቀብር ሥነ ሥርዓት የወጣ መርሐ ግብር
ተ/ቁ
|
ሰዓት
|
ክንውን
|
1
|
ጠዋት
12፡00
|
ረቡዕ ነሐሴ
16 ቀን 2004 ዓ.ም በኢትዮጵያ ገዳማትና አድባራት ለ10 ደቂቃ ያህል የደወል ድምጽ ይሰማል፡፡
|
2
|
ከቀኑ
5፡00 - 5፡30
|
በዚሁ
ዕለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት የቅዱስነታቸው አስከሬን በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣
የጠቅላይ
ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎችና መላው ሠራተኞች፣ የየድርጅቱና የየኮሌጁ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣
የአዲስ
አበባ ገዳማትና አድባራ አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎች፣ ሠራተኞች፣ መላ አገልጋዮች በክብር ታጅቦ ከመንበረ ፓትርያርክ
ወደ
ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቤተ ክርስቲያን ይገባል፡፡
|
3
|
ከቀኑ
5፡30 – 8፡30
|
የቅዳሴ ሥነ
ሥርዓት ይከናወናል፡፡
|
4
|
ከቀኑ
8፡30 – 12፡00
|
በብፁዓን
አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በክቡራን ምኒስቴሮችና የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ በገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣
በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
፣ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ በፖሊስ ሠራዊት ባንድ፣ በምዕመናንና ምዕመናት በክብር ታጅቦ
ወደ
መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጉዞ ያደርጋል፡፡ በዚህ ጉዞ ላይ የፖሊስ ሠራዊት ግራና ቀኝ በሰልፍ አስከሬኑን ያጅባል፡፡
የቅዱስነታቸው
አስከሬን በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዳረፈ የዕለቱ መርሐ ግብር በጸሎት ይዘጋል፡፡
|
5
|
ከምሽቱ
2፡00 -
ንጋቱ
12፡00
|
ረቡዕ
ለሐሙስ /16 ለ17/ አጥቢያ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ሌሊት ሙሉ ጸሎተ ማኅሌቱ ሲከናወን ያድራል፡፡
|
6
|
ሐሙስ
ጠዋት
12፡00 – 2፡30 |
ሐሙስ
ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት አስከሬኑ ባረፈበት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ቅዳሴ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አኀት አብያተ
ክርስቲያናት
ተወካዮች ባሉበት ይከናወናል
|
7
|
ሐሙስ
ጠዋት
2፡30 – 3፡00 |
ጸሎተ
ቅዳሴው እንዳበቃ የቅዱስነታቸው አስከሬን በክብር ታጅቦ ወደ አውደ ምሕረቱ ወጥቶ በተዘጋጀለት ቦታ ያርፋል፡፡
|
8
|
ሐሙስ
ጠዋት
2፡40 – 3፡10 |
በአውደ
ምሕረቱ ላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር እንግዶች በተዘጋጀላቸው
የክብር
ቦታ ይቀመጣሉ፡፡
|
9
|
3፡10
– 3፡20
|
የዐውደ
ምሕረቱ ፕሮግራም በጸሎት እንደተከፈተ ጸሎተ ወንጌሉ ይደርሳል፡፡
|
10
|
3፡20
– 3፡35
|
ሊቃውንተ
ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ ወረብ ያቀርባሉ፡፡
|
11
|
3፡35
– 3፡45
|
የሰንበት
ትምህርት ቤት ወጣቶች መዝሙር ያቀርባሉ፡፡
|
12
|
3፡45
– 4፡00
|
ሦስት
ሊቃውንት ቅኔ ያቀርባሉ፡፡
|
13
|
4፡00
– 4፡20
|
የቅዱስነታቸው
የሕይወት ታሪክ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወካይ ይቀርባል፡፡
|
14
|
4፡20
– 4፡30
|
የተከበሩ
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ንግግር፣
|
15
|
4፡30
– 4፡40
|
የተከበሩ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተወካይ ንግግር፣
|
16
|
4፡40
– 5፡00
|
የአኃት
አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮች፣ አባቶችና ተወካዮች ንግግር፣
|
17
|
5፡00
– 5፡05
|
የምሥራቅ
አብያተ ክርስቲያናት ተወካይ ንግግር፣
|
18
|
5፡05
– 5፡10
|
የሮም
ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ተወካይ የፖንቲፊካል ካውንስል ፕሬዝዳንት ካርዲናል ንግግር፣
|
19
|
5፡10
– 5፡15
|
የኖርዌ
ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ንግግር
|
20
|
5፡15
– 5፡20
|
የዓለም
አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ንግግር፣
|
21
|
5፡20
– 5፡25
|
የዓለም
ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሠላም ተወካይ ንግግር
|
22
|
5፡25
– 5፡30
|
የሁሉም
የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ንግግር፣
|
23
|
5፡30
– 5፡35
|
የኢትዮጵያ
የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ጉባኤ ተወካይ ንግግር፣
|
24
|
5፡35
– 5፡40
|
የቅዱስነታቸው
ቤተሰብ ተወካይ ንግግር፣
|
25
|
5፡40
– 6፡00
|
የቅዱስ
ሲኖዶስ ተወካይ ንግግር ያደርጋሉ
|
26
|
6፡00
– 6፡15
|
አስከሬኑ
በተዘጋጀለት ቦታ በክብር እንዳረፈ፤ የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ጸሎትና ቃለ ምዕዳን ተሰጥቶ ስንብት ይደረጋል፡፡
|
No comments:
Post a Comment
ማህበረ ቅዱስ አሞኒ