Thursday, August 23, 2012

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ


      የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሰኞ ዕለት ባደረገው ስብስባ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ዓቃቤ መንበር ሆነው መመረጣቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል አስታወቁ፡፡ 

ብፁዕ አቡነ ናትኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
     ብፁዕነታቸው ሰኞ ዕለት ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ምልዓተ ጉባኤው  ሰኞ ባደረገው ስብሰባ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር የሚመጡ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር እንግዶች በአግባቡ ማስተናገድ እንዲቻልና መንበርም ያለ ኃላፊ አንድም ቀን ማደር ስለማይገባ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 17 መሠረት በማድረግ ቀደምትነት ካላቸው ብፁዓን አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ ናትናኤል መመረጣቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ 

      ከዚህ በተያያዘ መልኩም ከዓቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤልና ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር በመሆን ሥራውን የሚያከናውኑ ሥራ አስፈጻሚዎች ምልአተ ጉባኤው መሰየሙን ስማቸውን ጠቅሶ አስረድተዋል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተሰየሙ ብፁዓን አባቶች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡ 

1. ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ

2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል

3. ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ

4. ብፁዕ አቡነ ሉቃስ

5. ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

6. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ

7. ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው፡፡
ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የሲዳማና ጌዴዎ አማሮ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በክልል ትግራይ የምዕራብ ሴቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የምሥራቅ ሀረርጌና የኦጋዴን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

No comments:

Post a Comment

ማህበረ ቅዱስ አሞኒ