Wednesday, February 29, 2012

የፕሮቴስታንት ዓለም በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት፣ በዲታ ወረዳ፣ ጋናደሬ ቀበሌ ሚገኘው የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያንን አቃጠሉ


‹‹ወንድሞች ሆይ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት፡፡›› (ያዕ 1 ፡ 2-3)

     ዛሬ ባለንበት ዘመን ቤተ ክርስቲያናችን በተለያ ፈተናዎች እየተፈተነች ትገኛለች፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ቅጥን በመድፈር ምዕመኖን በማገላታትና በመግደል እንዲሁም በክርስቶስ ደም የታነፀውን መቅደስ ማፍረስና ማቃጠል ይገኙበታል፡፡ ይህን የዳቢሎስ ተግባር ከዚህ በፊት በአክራሪ ሙስሊሞች የምናየው ሲሆን የዛሬው ግን የፕሮቴስታንት ዓለም

ዐቢይ ጾም

/በ ተክለ-ሰማዕት/
     ዐቢይ ጾም ከጾሞች ሁሉ የሚበልት ትልቁ ጾም ሲሆን ጾሙ «ዐቢይ» የተባለውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ በገዳመ ቆሮንቶስ ለአርባ ቀናት የጾመው ጾም እና ታላላቅ የተባሉት ሦስት ኀጢአቶች ማለትም ስስት፣ ትዕቢትና ፍቅረ ነዋይ ድል የተነሡበት ጾም ስለሆነ ነው፡፡ ምሳሌው፣ አብነቱና አርአያነቱ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤የማቴዎስ ወንጌል «አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ጦሞ በኋላ ተራበ፡፡» (ማቴ 4፡2) ይላልና፡፡ በዚህ ጦሙም ሰይጣን ወደ እርሱ ቀርቦ በሦስት ዋና ዋና ኀጢአቶች (አርእስተ ኀጣውእ) ፈትኖታል፡፡ ገና ከመጀመሪያው ለምን ይጾም ዘንድ ወደ ገዳም ለመሔድ ወደደ? ለምንስ ጾመ? ለምንስ በሰይጣን ተፈተነ? ብለን ስንጠይቅ ዲያብሎስ በእርሱ ላይ የሚያረቀው በደልና ኀጢያት ኖሮበት ሳይሆን እኛን ተጠመቁ ሊለን እንደተጠመቀ እርሱ ጾሞ እኛን ጹሙ ሊለን ጾመ የሚል መልስ እናገኛለን፡፡ እኛ በምንጾምበት ጊዜ ሰይጣን እንድንበላ፣ ጌታን እንድንፈታተንና ለሀብትና ለንብረት እንድንበረከክ ሊያደርገን እንደሚመጣና ያን ጊዜም በእግዚአብሔር ቃል ድል ልናደርገው እንምንችል ሊያስተምረን ሲል እርሱ ጾመ፡፡ በተለይም ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ጭምር እንጂ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ሊገልጥልን ይህን አደረገ፡፡

Tuesday, February 21, 2012

ከእኔ ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና ማቴ11፤ 29


/በመምህር ነቅዓጥበብ ከፍያለው/

ይህንን ቃል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናግሮታል፡፡ ለጊዜው በእግር ለሚከተሉት በኃላ ግን በሥራ ለሚመስሉት፤ ቃሉን ለሚጠብቁት፤ መስቀሉን ተሸክመው በሞት ለሚዛመዱት ለሐዋሪያት ይህንን ቃል ነግሮአቸዋል፡፡ ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት ሲያስተምር መፅሐፍትንና ጥቅሶቻቸውን ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን በስራ እየገለጠ ምግባርንም ያስተምራቸውም ነበር እንጂ፡፡ ጌታ እርሱ ያላደረገው(ያልሰራው) እኛን ብቻ ስሩ ያለው ምንም ነገር የለም፡፡ ስለዚህ መድሃኒታችን ‹‹ከእኔ ተማሩ›› በማለት በስራ የሚያሳየውን በጎ ስራውንም እንድንማር እየጋበዘ ነው፡፡ ከእርሱ የምንማረው ምንድነው? ብለን ስንጠይቅ

አሞኒ ዘዳግና ዘናህሶ ኢትዮጵያዊ


አሞኒ ዘዳግና ዘናህሶ ኢትዮጵያዊ በየካቲት 5 ቀን ተወለደ ትውልድ ሀገሩ አክሱም ነው፡፡ በተወለደም ጊዜ ሰይጣናት የወላጆቹን ቤት ከበቡ እሱም እንደተወለደ መንፈስ ቅዱስ ስለሞላበት በእጁ ቢያመለክት በአንድ ጊዜ 60 ሰይጣናት እንደ ጢስ በነው ጠፍተዋል፡፡ ተሸንፈዋል ስለዚህም አሞኒ ተብሎአል፡፡ አሞኒ ማለት

Monday, February 20, 2012

አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ አብሳዲ አረፉ

     ብፁዕ አቡነ አብሳዲ በተወለዱ በ82 ዓመታቸው ቅዳሜ የካቲት 10/2004 ዓ.ም. ለእሑድ አጥቢያ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ብፁዕነታቸው በትግራይ ክፍለ ሀገር ሽሬ በ1912 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በ1926 ዓ.ም ከሽሬ ወደ ኤርትራ በመሔድና ደብረ ማርያም ገዳም በመግባት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በመከታተል ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ይስሐቅ፣ ቅስናን ደግሞ ከአቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል፡፡ በደብረ ማርያም ገዳም ውስጥ በቆዩባቸው ዐሥር ዓመታት ውስጥ ከአንድ መቶ በላይ ዲያቆናትንና ካህናትን በማስተማር አፍርተዋል፡፡

በቅዱስ ሲኖዶስና በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል የተካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት ተፈፀመ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል በአሜሪካ - አሪዞና ግዛት ከየካቲት 4 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሄድ የሰነበተው ሁለተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይትተፈፀመ፡፡  መግለጫም አውጥቷል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንንይጫኑ።

Friday, February 10, 2012

አባ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ

አባ ሙሴ ጸሊም በትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን አስቀድሞ በውንብድና ኑሮ ሕይወቱን ይገፋ ነበር፡፡ ሰዎች ከገድሉ የተነሳ ያደንቁታል፡፡እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበርና እርሱ በሥጋው ጠንካራ ፤ በሥራውም ኃይለኛ ነበር፡፡ አባ ሙሴ ጸሊምም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ፤ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ፡፡ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ኖር ቀጠለ፡፡ ከገድሉ ብዛት የተነሳ አረጋውያን መነኮሳት በሚተኙ ጊዜ ቤቶቻቸውን በመዞር ውሃ መቅጃዎቹን ወስዶ ውሃ ነበር ፡፡ አባ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኮሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ፤ ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው፡፡ ያንጊዜም ተነሳ ሰይፉንም ታጥቆ ወደአስቄጥስ ገዳም ሄደ ፤ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው ፤ አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ አለው ፡፡ አባ ኤስድሮስም ወደአባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው፡፡ እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተማረው እንዲህም አለው