Monday, September 24, 2012

የመስቀል በዓል ክርስቲያናዊ አከባበር


ዲ/ን አሉላ መብራቱ
    ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዘጠኙ የጌታችን ንዑሳን በዓላት አንዱ መስከረም 17 የሚከበረው የመስቀል በዓል ነው፡፡ መስቀል የሰላማችንና የድኅነታችን የመቀደሳችን አርማ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጆች ለማዳን የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት መስዋዕትነት የከፈለበት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት መንበር ሲሆን አምላካችንን የመንመለከትበት መስታወት ነው።

  ይህ ዕለት ከ300 ዓመታት በላይ ጠፍቶ የነበረውን ቅዱስ መስቀል በንግሥት ዕሌኒ አማካኝነት መገኘቱን የምንዘክርበት በዚህም ደስ የምንሰኝበት ዕለት ነው፡፡ በዓሉ በምን ምክንያት እንደሚከበር ታሪኩን፣ በቅድሰት ቤተ ክርስቲያን ካህናቱና ምእመናን በአንድነት በመሆን እንዴት እንደሚያከብሩት፣ ምእመናን በየአካባቢያቸው በየቤታቸው እንዴት እንደሚያከብሩት ቀጥለን እንመልከት፡፡

Thursday, August 23, 2012

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ


      የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሰኞ ዕለት ባደረገው ስብስባ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ዓቃቤ መንበር ሆነው መመረጣቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል አስታወቁ፡፡ 

ብፁዕ አቡነ ናትኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
     ብፁዕነታቸው ሰኞ ዕለት ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ምልዓተ ጉባኤው  ሰኞ ባደረገው ስብሰባ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር የሚመጡ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር እንግዶች በአግባቡ ማስተናገድ እንዲቻልና መንበርም ያለ ኃላፊ አንድም ቀን ማደር ስለማይገባ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 17 መሠረት በማድረግ ቀደምትነት ካላቸው ብፁዓን አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ ናትናኤል መመረጣቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ 

      ከዚህ በተያያዘ መልኩም ከዓቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤልና ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር በመሆን ሥራውን የሚያከናውኑ ሥራ አስፈጻሚዎች ምልአተ ጉባኤው መሰየሙን ስማቸውን ጠቅሶ አስረድተዋል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተሰየሙ ብፁዓን አባቶች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡ 

Wednesday, August 22, 2012

የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት የዓለም የሰላም አምባሳደር የቀብር ሥነ ሥርዓት የወጣ መርሐ ግብር

"ለፈራሔ እግዚአብሔር ይሤኒ ደኅሪቱ፣ ወይትባረክ ዕለተ ሞቱ"
"እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ፍፃሜው ያምራል፡፡ በሚሞትበትም ቀን ይከበራል" ሲራ. 113፡፡
     የብፁዕ ወቅዱስ / አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት የዓለም የሰላም አምባሳደር የቀብር ሥነ ሥርዓት የወጣ መርሐ ግብር

/           
       
          ሰዓት

                                                    ክንውን
1
ጠዋት 1200 
 ረቡዕ ነሐሴ 16 ቀን 2004 . በኢትዮጵያ ገዳማትና አድባራት 10 ደቂቃ ያህል የደወል ድምጽ ይሰማል፡፡                   
2
ከቀኑ 500 - 530
በዚሁ ዕለት ከቀኑ 500 ሰዓት የቅዱስነታቸው አስከሬን በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣
የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎችና መላው ሠራተኞች፣ የየድርጅቱና የየኮሌጁ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ 
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራ አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎች፣ ሠራተኞች፣ መላ አገልጋዮች በክብር ታጅቦ ከመንበረ ፓትርያርክ 
ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቤተ ክርስቲያን ይገባል፡፡
3
ከቀኑ 530 – 830
 የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ይከናወናል፡፡
4
ከቀኑ 830 – 1200

Saturday, August 18, 2012

በደብረ ታቦር ክብሩን አየን

     ደብረ ታቦር በግእዝ ቋንቋ ሲሆን የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ (ማቴ 7÷1-8) የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ 
     ቤተ ክርስቲያናችን ከሚከበሩት ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ደብረ ታቦር ነው፡፡ በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን 
በድምቀት ይከበራል፡፡ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምእራባዊ ደቡብ በኩል 10ኪ.ሜ ርቆ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ይህ ተራራ ከባሕር ጠለል 572 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ «ባርቅ የተባለው ጦረኛ ሕዝበ እስራኤልን ይዞ በመዝመት ሲራ የተባለውን የሕዝብ ጠላት በታቦር ድል ነስቶ አሸንፏል» (መሳፍንት.4፡6-14)፡፡ 
     ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል፡፡ ክንድህ ከኃይል ጋር ነው ሲል በመዝሙር 88፡12 ስለ ታቦር ተራራ ዘምሯል፡፡ የታቦር ተራራ በገሊላ ከሚገኙ ተራራዎች አንደኛው ሲሆን በዛብሎን ክፍል ውስጥ ለሚኖሩ ልጆች የተሰጠ ቦታ ነው፡፡ 1ኛ ዜና.6፡77 ሐዲስ ኪዳን ግን ረጅም ተራራ ከማለት በስተቀር ታቦር ብሎ ስሙን አይጠራውም፡፡ ሆኖም ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ክብሩን እንደገለጠና የዚህም ተራራ ስም ታቦር መሆኑን ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው ገልጠዋል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም ይህንን ረጅም ተራራ ደብረ ታቦር እያለ በድጓው አስፋፍቶ ጽፏል፡፡ 
     ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ረጅም ተራራ የወጣው ብርሃነ መለኮቱን ክብሩን ለመግለጽ ነው፡፡ በዚህ ተራራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙሴና ከኤልያስ ጋር ተነጋግሮአል፡፡ እነዚህም ሁለት ታላላቅ ሰዎች በበብሉይ ኪዳን ጊዜ ስለ ክርስቶስ ትንቢት የተናገሩ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ያስተማሩ ቅዱሳን ነቢያት ነበሩ፡፡

የቅዱስ ፓትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም እንደሚፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ፡፡




      የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች የሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሥርዓተ ቀብር ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እንደሚፈጸም ዛሬ ጥዋት ቅዱስ ሲኖዶስ ተሰብስቦ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶበታል፡፡ 

Thursday, August 16, 2012

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አረፉ


ብፁዕነታቸው ያለፈው እሁድ በቅዳሴ ላይ እንደነበሩ ከውስጥ አዋቂዎች ለመረዳት የቻልን ሲሆን  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ነሐሴ 8/2004ዓ.ም ማምሻውን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ለህክምና ገብተው በዶክተሮች ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ትላንት ለሊት ሊያርፉ ችለዋል፡፡  
የአባታችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን አሜን፡፡

Friday, August 10, 2012

ፍልሰታ ለማርያም

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ 
          ፍልሰታ ማለት ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር የነበሩበትን ሀገር ለቆ ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ መፍለስ ማለት ነው፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሲባልም የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሰማኒ ወደ ገነት መፍለስን በኋላም በገነት በእፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገርነው፡፡ 
       እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 64 ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ በሞት ከተለየች በኋላ እንደ አንድ ልጅዋ ሞታ መነሣቷንና እርገቷን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት ከነሐሴ 1 እስከ 16 የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ፍልሰታ ከሰባቱ አበይት አጽዋማት አንዱ ሆኖ በቀኖና እንዲጾም ከተወሰነበት ጊዜ ጀምሮ ምእመናን ይጾሙታል፡፡
          እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና “እም ሊባኖስ ትወጽእ መርዓት፡፡ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች” ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡ ግንቦት አንድ ቀን ሊባኖስ በምትባል ወረዳ በብጽአት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰፊው ያስረዳል፡፡ በጾም በጸሎት በአስተብቁኦት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም ማኅደረ እግዚአብሔር ሆናለች፡፡ 

Monday, June 18, 2012

የሰኔ ቅዱስ ሚካኤል ድርሳን

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን በባሕርይ በህልውና አንድ አምላክ ብለን አምነን ሰኔ በባተ በዓሥራ ሁለት ቀን የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ እንዲከበር እንናገራለን ልመናው አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
እግዚአብሔርን እጅግ አድርጐ የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር።
ለዚህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውም ርኅራኄ የሌለው በሱም ላይ ጥላቻ ያደረበት በለጸጋ ጐረቤት ነበረው የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር።
ይህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውዬ በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ።

Monday, May 7, 2012

አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤


አንቺ ምሥራቅ ነሽ ልጅሽም እውነተኛ ፀሐይ ነው። /ድጓ/

ሊቀ ጠበብት ሐረገወይን አገዘ
     የቤተ ክርስቲያን አባት የእግዚአብሔር ወዳጅ ሆኖ ስለእመቤታችን ያልዘመረ ፣ያላመሰገነ ያልጻፈ የለም።ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የሚገባውን ንጽጽራዊ ምሳሌ ለሚገባት ወላዲት አምላክ ሰጥቶ አመስጥሮ ዘመረ። እንዲህ በማለት “ አንቺ የብርሃን መውጫ ምሥራቅ ነሽ፤ልጅሽም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን እውነተኛ ፀሐይም ነው።”

Monday, April 30, 2012

ቅዱስ ጊዮርጊስ

       በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፫ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፻፴፫ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፻፴፪ ዕለታት ይቀራሉ።
       የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሞተበትን ዕለት ማስታወሻ አድርጋ ትዘክረዋለች፡
        “በዘአዕረፈ እግዚእየ ማር ጊዮርጊስ ገብሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዘተከለለ ወርኁ በጽርዕ ጵንፍልዮ ስሙ ዘበትርጓሜሁ ሚያዝያ አመ ፳ወ፫ ለሠርቅ ወዕለቱሂ ዓርብ በጊዜ ፱ቱ ሰዓት አሜን።”
                “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ጌታዬ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያረፈበት ሰማዕትነቱን የፈጸመበት ወሩ በጽርዕ ጵንፍልዮ ይባላል። ይኸውም ሚያዝያ ነው ወሩ በባተ በሃያ ሦስት ቀን ዕለቱም ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ነው አሜን።”

Friday, April 27, 2012

የጎንደር ደብረ ኀይል ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤት ግንባታ ውል ተፈረመ፡፡


ሚያዝያ 18/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
Gedamate 3ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘውን የደብረ ኀይል ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤትን በ4.6 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ሚያዚያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. የግንባታ ውል ስምምነት ከአስማማው አያሌው ሕንጻ ሥራ ተቋራጭ ጋር ተፈራረመ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ልማት ዋና ክፍል አስተባባሪነት የሚከናወነው ይኸው ፕሮጀክት ማኅበረ ቅዱሳንን በመወከል የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኀ/ማርያምና የሕንፃ ሥራ ተቋራጩ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስማማው አያሌው አማካይነት የፊርማ መርሐ ግብሩ ተፈጽሟል፡፡

Thursday, April 5, 2012

ከክህነት ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት


(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ዓ.ም፤ ኤፕሪል 5/2012)በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አዲስ ሊቀ ጳጳስ ተሹሞ ተልኳል ከተባለበት ከጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ በችግር ላይ ይገኛል። ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሀ/ስብከቱ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በቃለ ዓዋዲው መሠረት የመረጡትን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አልቀበልም ከማለት አልፈው ካህናቱን በሙሉ ማስፈራራት እና አንዳንዶቹንም "አውግዣለሁ" ማለት ጀምረዋል። ይህም መነሻ ሆኖን "ካህናትን ከክህነታቸው ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች"፣ በደፈናው ከመሬት ተነሥተው "ክህነት ይዣለሁ" ስለሚሉ አቡነ ፋኑኤልን ስለመሳሰሉ ጳጳሳት አስቀድመው በቅዱሳን አበው የተሠራውን ሕግ በተመለከተ ፍትሐ ነገሥቱ የሚለውን ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን።
+++

ከ175 በላይ በገና ደርዳሪዎች ሊመረቁ ነው


በማኅበረ ቅዱሳን ልማት ተቋማት አስተዳደር የአቡነ ጎርጎርዮስ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል ከ175 በላይ በገና ደርዳሪዎችን መጋቢት 29 ቀን 2004 ዓ.ም. እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡
የትምህርትና ሥልጠና ማእከሉ ሓላፊ አቶ አብዮት እሸቱ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ በፊት በዜማ ማሠልጠኛ ክፍሉ በርካታ በገና ደርዳሪዎችን ማስመረቁን ገልጸው የአሁኖቹን ተመራቂ ጨምሮ ከ1200 በላይ በገና ደርዳሪዎቹን በማእከሉ ማሠልጠኑን ገልጸዋል፡፡

መጋቢት 29 ቀን 2004 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 በሚካሔደው የምረቃ መርሐ ግብር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተመራቂ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ የገለጹት የማእከሉ ሓላፊ ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የቤተ ክርስቲያንን እምነት፣ ሥርዐት፣ ትውፊትና ዶግማ ተጠብቆ ወደ ቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ የተሰጠውን ሓላፊነት እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል በአሁኑ ወቅት ከ KG እስከ 9ኛ ክፍል ተማሪዎችን በቀለም ትምህርት እያስተማረ የሚገኝ ሲሆን በዜማና በአብነት የትምህርት መስክ ሥልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ አቶ አብዮት ገልጸዋል፡፡

Friday, March 30, 2012

የለገዳዲ የቅድስት ኪዳነ ምህረት ፅላት ተአምር

     /በደረጀ ነጋሽ ዘወይንዬ/
        ዓርብ የካቲት 16/2004 ዓ.ም በጠዋቱኑ እጅግ በርካታ ምዕመናን በቅርብ በተገኘው የለገዳዲ ኬማ ዋሻ ፍልፍል ቤተክርስቲያን በአግራሞትና አድናቆት ተሰብስበዋል፡፡ በአካባቢው ድንኳኖች ተጥለዋል፡፡ አንዳንዶች ዋሻ ሲጎበኙ ሌሎች ደግሞ ፀበል ይጠመቃሉ፡፡ አንዳንዶች ይፀልያሉ ሌሎች ደግሞ ይነጋገራሉ፡፡ የከተማው ወይዛዝርት ለመስተንግዶው ይፋጠናሉ፡፡ እሺ ብላ ከዋሻው ትወጣ ይሆን? ወደ ዋሻው ካልተመለሰችስ? ብቻ የየራሳቸውን አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ ለገዳዲ ከተማ ከአዲስ አበባ 25ኪ.ሜ ርቀት ላይ በኮተቤ መስመር ለገጣፎን አልፈው የምትገኝ ከተማ ስትሆን በወታደር ማሰልጠን፣ በትምህርት ስርጭት እና በውሃ አቅርቦት ትታወቃለች፡፡ ለገዳዲ ማለት በኦሮምኛ የጠጅ ወንዝ ማለት ነው፡፡ በዚህ ቦታ ገበሬዎች የፈረሰ ቤተክርስቲያን፤ ፀበል ይገኛል፣የአባቶቻችን መካነ መቃብር እዚህ ነው እያሉ በጉልበት ያለፍቃዳቸው አስፈራርተዋቸው ቦታውን ለኤንጂኦ ተሰጠ፤ አራት ዓመት ምንም ሳይሰራበት ቆየ፡፡ በብዙ ተንኮል ያገኘውን የቤተክርስቲያን የሃይማኖት ቦታ ሊሠራበት አጥር ማጠር ሲጀመር ዋሻ እንዳለ ለአባቶቻችን በህልም ታያቸው፡፡ ወደ ቦታው ሲሄዱ ከስር ከወንዝ አደገኛ ገደል ላይ ትንሽ ቀዳዳ ዐዩ፡፡ አፈር ሲቆፍሩ ፍልፍል ዋሻውን አገኙ፤ ዋሻው በሶስት ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያው ቤተ መዛግብት፣ ቤተልሔም(አፅንኦባእት)፣ የተጋድሎ ቦታ አፅመቅዱሳን የተለያዩ መገልገያዎች እና ቅርሶች ይገኛሉ፡፡
   

Monday, March 26, 2012

የለገዳዲ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ፅላት ከድንኳን ወደ መቃኞ ገባች


     (ማህበረ ቅዱስ አሞኒ መጋቢት 17/2004) ለገዳዲ ዋሻ ኪዳነ ምህረት በኮተቤ መስመር ከአዲስ አበባ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከለገጣፎ ከተማ አለፍ ብላ የምትገኝ ስትሆን እናት አባቶቻችን በሐይማኖት ጠብቀው ጽላተ ሙሴን ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያን ፈልፍለው ለእኛ ለልጆቻቸው ካቆዩልን የበረከት ስፍራ አንዱ ነው፡፡ በዚህ የበረከት ስፍራ የፈረሰና ቅርፁ ያልጠፋ ቤተ መቅደስ፣

Wednesday, March 21, 2012

በአሰቦት ገዳም የአብነት ተማሪ የሆነው የ7 ዓመቱ ሕፃን ናታን አንበስ ባልታወቁ ታጣቂዎች በ3 ጥይት ተመትቶ ተገደለ


በምዕራብ ሐረርጌ ሜኤሶ ወረዳ በአሰቦት ሥላሴና አባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ገዳም የአብነት ተማሪ የሆነው የ7 ዓመቱ ሕፃን ናታን አንበስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በ3 ጥይት ተመትቶ መገደሉን የገዳሙ ዋና መጋቢና ምክትል አበምኔት አባ ዘወልደ ማርያም ገለጹ፡፡ ከአባ ሳሙኤል ገዳም በተወሰኑ ሜትሮች ርቀት ላይ ከእናቱ ጋር ወደ ገዳሙ በመውጣት ላይ እያለ ከእናቱ እጅ ቀምተው በመውሰድ ፊት ለፊቷ በሦስት ጥይት ገድለውት ሊያመልጡ ችለዋል፡፡ በእናትየው ጩኸትና በጥይት ድምጽ የተደናገጡት መነኮሳት ገዳዮቹን ለመያዝ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

የገዳሙ መነኮሳት እንደገለጹት

የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ገዳም ለዘለቄታው በእሳት በማይጠቃበት መልኩ ለማቋቋም



ገዳሙ በመከላከሉ ሥራ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የአካባቢ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ እነሆ ገዳሙን መርዳት የምትፈልጉ ምእመናን የገዳሙ የባንክ አድራሻ የሚከተለው ነው፡፡
ለዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ደብረ ዘይት ቅርንጫፍ
የባንክ ቁጥር 19789
ደብረ ዘይት
(በአካውንቱ የላካችሁ ምእመናን በኢሜይል አድራሻ dkibret@gmail.com መላካችሁን ብትገልጡልን ለገዳሙ መልእክቱን ለማቀበል ይረዳናል)
እስካሁን በሁለት ቦታዎች ከሚታየው ጢስ በቀር የተነሣ እሳት የለም፡፡ እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቷል፤ ድካማችንንም ተቀብሏል፡፡

በአራት ቀን ውስጥ ከተቃጠለው የዝቋላ ገዳም ደን በከፊል

 

የዝቋላን ገዳም እንታደግ!!!

በዝቋላ ገዳም እና አካባቢው ደን ላይ የተነሣውን እሳት ለማጥፋት ለሚደረገው ጥረት ለማድረግ የግል ልገሳዎን ይስጡ በሚል ሐሳብ በማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣ በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና በማኅበረ በዓለ ወልድ አስተባባሪነት በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ኦርቶዶክሳውያን አስቸኳይ የገንዘብ ማሰባሰብ ሒደት ላይ እንገኛለን። ዓላማው በአሁኑ ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ከየአካባቢው በነቂስ ለወጣው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ጉሮሮውን ማርጠቢያ ውኃ፣ ጉልበቱን መደገፊያ ዳቦ ማቅረቢያ እንዲሆን የታሰበ ነው። በባዶ እጁ፣ በቅጠል እና በአፈር ቋያ እሳት ለማጥፋት እየታገለ ላለው ወገን አለኝታነታችንን ለመግለጽ ነው። ስለዚህም በሚከተለው አድራሻ እየገባችሁ የግላችሁን ልገሳ መስጠት የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናስታውቃለን። http://zekuala.mahiberekidusan.org/  

Tuesday, March 20, 2012

በአሁኑ ሰዓት በዝቋላ ገዳም ነገሮች እየተረጋጉ ነው ተባለ

 
     አልፎ አልፎ ገደሉ ሥር ከሚታየው ጭስ በስተቀር ይህ ነው የተባለ የጎላ እሳት አሁን የለም፡፡ ገዳሙ ምንም እንኳን  በአካባቢው ያለው ሙቀት ቀትር ላይ ሲጨምር የሚሆነው ባይታወቅም በአሁኑ ደረጃ ግን እሳቱ ከገደሉ በላይ እንዳይወጣ አካባቢውን የማጽዳት  እና    የእሳት መከላከያ የመሥራቱ ሥራ ተጠናክሯል፡፡

እሳቱ ሊቆም አልቻለም


Crater lake 2 

     በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የደን ቃጠሎ እየተባባሰ ነው፡፡ ዛሬ በደረሰን መረጃ በትላንትናው እለት ከአዲስ አበባ፣ ከደብረ ዘይት፣ ከናዝሪት እና ከተለያዩ ቦታዎች የሄዱ ምዕመናን እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ቢገኙም በጣም አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የደን ቃጠሎው ከገዳሙ በግምት ከ300 - 400 ሜትር ርቀት ዐርብ ዕሮብ በሚባለው የተራራው ገጽ በኩል፣ ጠበሉ የሚገኝበትን ጥቅጥቅ ያለ ጫካ እየከበበ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ መነኮሳቱ ለኦሮሚያ ፖሊስ፣ ለፌደራል ፖሊስና ለአየር ኀይል እንዲሁም ለምእመናን የድረሱልን ጥሪ በማሰማት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡት በጎ ፈቃደኞች መጥረቢያ፣ አካፋ እና መቆፈርያ እየያዙ ቢመጡ የመከላከሉን ሥራ የተቃና የሚያደርግ ሲሆን በተለይም አቅና የሚባለው የመቆፈርያ ዓይነት ለዚህ ሥራ አመቺ በመሆኑ ይህንን መሣርያ ይዘው እንዲመጡ ጥሪ አድርገዋል፡፡ በቃጠሎ ጉዳት የደረሰባቸው ምእመናን እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በከፍተኛ ጥምና ረሃብ ላይ ለሚገኙ ምእመናን ውኃና ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው ጭምር ገልጸዋል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ምህረቱን ያውርድልን አሜን!!!

Monday, March 19, 2012

ክተት ወደ ዝቋላ

Mount Zuqualla from the North 

ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳምደን በመንደድ ላይ መሆኑን የገዳሙ አባቶች እየተናገሩ ነው፡፡ እሳቱ መንደድ ከጀመረ ወደ ሃያ አራት ሰዓት ሊጠጋ ነውም ተብሏል፡፡ መንግሥት ከአካባቢው የውኃ ቦቴዎችን እና ወታደሮችን በማንቀሳቀስ ውኃውን ለማጥፋት ጥረት እያደረገ ቢሆንም እሳቱ ግን ወደ ገዳሙ በመጠጋት ላይ ነው፡፡
አሁን አማራጫችን አንድ ብቻ ነው፡፡ የዝቋላን ገዳም ከማጣታችን በፊት ያለንን ነገር ሁሉ ይዘን በተገኘው ትራንስፖርት ወደ ዝቋላ መትመም ብቻ፡፡ ወንበር ማርያም ድረስ የውኃ ቦቴዎቹ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን ባገኘነውዕቃ ሁሉ ውኃውን ይዘን በመውጣት መረባረብ፡፡ ያለበለዚያ ግን የዝቋላ አቡነገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ወደ ታሪክነት ይቀየራል፡፡
እነሆ ክርስትናችን የሚፈተንበት፣ ኢትዮጵያዊነታችንም የሚለካበት ጊዜ መጣ፣በእሳት ተቃጥለው ያቆዩትን ገዳም ከእሳት ማዳን ካልቻልን እንግዲህ የኛ መኖር ትርጉሙ ምንድን ነው?
መኪኖች ያሏችሁ አንቀሳቅሱ፣ ጉልበት ያላችሁ ተንቀሳቀሱ፣ ሌላም አማራጭያላችሁ በፍጥነት ተጓዙ፣እሳቱን በእምነት እንቅደመው፡፡