Tuesday, March 20, 2012

እሳቱ ሊቆም አልቻለም


Crater lake 2 

     በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የደን ቃጠሎ እየተባባሰ ነው፡፡ ዛሬ በደረሰን መረጃ በትላንትናው እለት ከአዲስ አበባ፣ ከደብረ ዘይት፣ ከናዝሪት እና ከተለያዩ ቦታዎች የሄዱ ምዕመናን እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ቢገኙም በጣም አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የደን ቃጠሎው ከገዳሙ በግምት ከ300 - 400 ሜትር ርቀት ዐርብ ዕሮብ በሚባለው የተራራው ገጽ በኩል፣ ጠበሉ የሚገኝበትን ጥቅጥቅ ያለ ጫካ እየከበበ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ መነኮሳቱ ለኦሮሚያ ፖሊስ፣ ለፌደራል ፖሊስና ለአየር ኀይል እንዲሁም ለምእመናን የድረሱልን ጥሪ በማሰማት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡት በጎ ፈቃደኞች መጥረቢያ፣ አካፋ እና መቆፈርያ እየያዙ ቢመጡ የመከላከሉን ሥራ የተቃና የሚያደርግ ሲሆን በተለይም አቅና የሚባለው የመቆፈርያ ዓይነት ለዚህ ሥራ አመቺ በመሆኑ ይህንን መሣርያ ይዘው እንዲመጡ ጥሪ አድርገዋል፡፡ በቃጠሎ ጉዳት የደረሰባቸው ምእመናን እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በከፍተኛ ጥምና ረሃብ ላይ ለሚገኙ ምእመናን ውኃና ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው ጭምር ገልጸዋል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ምህረቱን ያውርድልን አሜን!!!

No comments:

Post a Comment

ማህበረ ቅዱስ አሞኒ