በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፫ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፻፴፫ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፻፴፪ ዕለታት ይቀራሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሞተበትን ዕለት ማስታወሻ አድርጋ ትዘክረዋለች፡
“በዘአዕረፈ እግዚእየ ማር ጊዮርጊስ ገብሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዘተከለለ ወርኁ በጽርዕ ጵንፍልዮ ስሙ ዘበትርጓሜሁ ሚያዝያ አመ ፳ወ፫ ለሠርቅ ወዕለቱሂ ዓርብ በጊዜ ፱ቱ ሰዓት አሜን።”
“የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ጌታዬ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያረፈበት ሰማዕትነቱን የፈጸመበት ወሩ በጽርዕ ጵንፍልዮ ይባላል። ይኸውም ሚያዝያ ነው ወሩ በባተ በሃያ ሦስት ቀን ዕለቱም ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ነው አሜን።”

ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘውን የደብረ ኀይል ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤትን በ4.6 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ሚያዚያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. የግንባታ ውል ስምምነት ከአስማማው አያሌው ሕንጻ ሥራ ተቋራጭ ጋር ተፈራረመ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ልማት ዋና ክፍል አስተባባሪነት የሚከናወነው ይኸው ፕሮጀክት ማኅበረ ቅዱሳንን በመወከል የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኀ/ማርያምና የሕንፃ ሥራ ተቋራጩ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስማማው አያሌው አማካይነት የፊርማ መርሐ ግብሩ ተፈጽሟል፡፡.jpg)